Job Description

Back to all opportunities

Dashen Bank

Verified

Driver

Addis Ababa - ethiopia

full-time

permanent

Posted

9 hours ago

Experience

2 Years

Deadline

Oct. 23, 2026 (10 days left)

ሥራው በአጠቃላይ

የመኪና ነጂ ደረጃ አንድ ዋና ተግባር ደብዳቤዎችን፣ መልዕክቶችንና ሌሎች ዕቃዎችን ወደ ቢሮ ማድረስ ወይም ወደ ተለያዩ ድርጅቶችና መሥሪያ ቤቶች መላክ ሲሆን፣ በተጨማሪም የድርጅቱን የአገልግሎት ተሽከርካሪዎች በደህንነትና በተገቢው ሁኔታ ማሽከርከር፣ የተሽከርካሪውን ዝግጁነት መጠበቅ እና አነስተኛ ጥገናዎችን ማከናወን ነው።

የትምህርት እና የሙያ ዝግጅት

በቀድሞው 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ያጠናቀቀች ወይም በአዲሱ 10ኛ ክፍል፣ 10+1 በአውቶ ሜካኒክ ወይም በኦቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ያጠናቀቀ/ያጠናቀቀች።

ደረጃ 4/ደረጃ 3 መንጃ ፈቃድ ወይም ሕዝብ 1/ሕዝብ 2 መንጃ ፈቃድ ያለው/ያላት።

የሥራ ልምድ

ሁለት (2) ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ያላት።

ተግባር እና ኃላፊነቶች

የትራፊክ ሕጎችንና የመንገድ ላይ ሥነ ሥርዓቶችን በማክበር ተሽከርካሪውን ማሽከርከር።

በክልሉ ትራንስፖርት መገናኛ ቢሮ በተፈቀደው ሕጋዊ መንገድ የሚመደብለትን/የሚመደብላትን ተሽከርካሪ ብቻ ማሽከርከር።

በሚመለከተው ኃላፊ ወይም አለቃ ትእዛዝ መሠረት የድርጅቱን የአገልግሎት መኪናዎችና ሌሎች የባንኩን ተሽከርካሪዎች የማሽከርከር አገልግሎት መስጠት።

ደብዳቤዎችን፣ መልዕክቶችንና ሌሎች ዕቃዎችን በታዘዘው መሠረት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ማድረስ።

በየቀኑ የሚጓዘውን የኪሎ ሜትር ርቀት በትክክል መመዝገብ።

የዕለት ተዕለት ሥራውን/ሥራዋን ከመጀመሩ/ከመጀመሯ በፊት የተሽከርካሪውን ዝግጁነት መፈተሽ። ይህም የዘይት መጠን፣ የውሃ መጠን፣ የፍሬን ደህንነት፣ መብራቶችና ሌሎች አስፈላጊ ክፍሎችን ማረጋገጥን ይጨምራል።

ተሽከርካሪውን በንጽህና በመጠበቅ ሁልጊዜ ለሥራ ዝግጁ ማድረግ።

አነስተኛ ጥገናዎችን ማከናወን፤ ለምሳሌ ስፓርክ ፕላጎችን ማጽዳት፣ ካርቦሬተርን ማስተካከልና አንዳንድ የተበላሹ ክፍሎችን መጠገን።

አደጋዎች ወይም ያልተለመዱ አጋጣሚዎች ሲከሰቱ ለሚመለከታቸው ኃላፊዎችና ለቅርብ አለቃው/አለቃዋ በፍጥነት ማሳወቅ።

ተሽከርካሪው ጋራዥ ሲገባ የጥገና ሥራዎችን በመከታተል ጥገናው በሚፈለገው ደረጃና በአጥጋቢ ሁኔታ መከናወኑን ማረጋገጥ።

ለባንኩ ሥራዎች የተረከባቸውን/የተረከበቻቸውን ዕቃዎችና መሣሪያዎች በጥንቃቄ መያዝና በአግባቡ መጠቀም።

ከጊዜ ወደ ጊዜ በቅርብ አለቃው/አለቃዋ በሚሰጠው ትእዛዝ መሠረት ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ማከናወን።

Apply for this Job

How to apply

https://geezjobs.com/job-detail/driver-dashen-bank-2

An error has occurred. This application may no longer respond until reloaded. Reload 🗙