About the Job
ስለ ኩባንያው
መሠረት ማሬ ሶላር አስመጪ፣ ተከላ እና ገጣሚ
በኢትዮጵያ የታዳሽ ኢነርጂ ዘርፍ ግንባር ቀደም ተቋም ሲሆን፣
ጠንካራ እና ራሱን የቻለ የገጠር ማህበረሰብን የመፍጠር
ታላቅ ራዕይ ሰንቆ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው። ድርጅታችን በገጠሩ የሀገራችን ክፍሎችና በግብርና ማዕከላት ዙሪያ የሚኖሩ ማህበረሰቦችን ሕይወት ለመለወጥና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ፤ ንጹህ፣ ዘመናዊና አስተማማኝ የሶላር ኃይል አማራጮችን፣ የሶላር የውሃ መሳቢያ ፓምፖችን (Solar Water Pumps) እንዲሁም ለግብርናና ለተለያዩ የምርት ተግባራት የሚውሉ የሶላር ቴክኖሎጂዎችን በስፋት ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል።
ድርጅታችን ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት 2 የስራ መደቦች ብቁ እና ባለሙያ ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡
የስራ ቦታዎች፡
ምስራቅ ጉራጌ ዞን (ቡታጅራ አካባቢ)
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል (አርባ ምንጭ አካባቢ)
የሲዳማ ክልል አካባቢ
ኦሮሚያ ክልል (ዝዋይ፣ መቂ እና ሞጆ አካባቢዎች)
- የቴክኒክና ጥገና ባለሙያ
የስራ ክፍል፡
የቴክኒክ ክፍል |
ብዛት፡
ለእያንዳንዱ ቦታ 1 (በአጠቃላይ በ4 የስራ ቦታዎች 4 ክፍት የስራ መደቦች)
ዋና ዋና ኃላፊነቶች፡
የሶላር ፒቪ (PV) ሲስተሞችን፣ የሶላር የውሃ ፓምፖችን እና ለምርታማነት የሚውሉ መሳሪያዎችን መግጠም፣ መፈተሽ እና ስራ ማስጀመር፡፡
መደበኛ እና ከሽያጭ በኋላ ጥገናዎችን ማከናወን፣ ብልሽቶችን መለየትና መጠገን፡፡
AC/DC የኤሌክትሪክ ሽቦ ዝርጋታን፣ የቧንቧ (conduit) ተከላን፣ የምድር መስመር (earthing) እና የደህንነት ምርመራዎችን ማድረግ፡፡
ለደንበኞች ተግባራዊ መመሪያ እና የተጠቃሚ ስልጠና መስጠት፣ እንዲሁም ንብረቶችን (inventory) በአግባቡ መያዝ፡፡
- የሶላር ማርኬቲንግ ተወካይ
የስራ ክፍል፡
የሽያጭ እና ማርኬቲንግ ክፍል |
ብዛት፡
ለእያንዳንዱ ቦታ 1 (በአጠቃላይ በ4 የስራ ቦታዎች 4 ክፍት የስራ መደቦች)
ዋና ዋና ኃላፊነቶች፡
የሶላር ምርቶችን፣ ከዋናው መስመር ውጭ ያሉ ሲስተሞችን እና የግብርና ሶላር የውሃ ፓምፖችን ለአርሶ አደሮች፣ ማህበራት እና ተቋማት ማስተዋወቅ፡፡
የምርት ዝርዝር መግለጫዎችን፣ የኢነርጂ ጥቅሞችን እና ከኢንቨስትመንቱ የሚገኘውን የፋይናንስ ትርፍ (ROI) ማስረዳት፡፡
የአካባቢ ማስተዋወቂያ ዝግጅቶችን፣ የማህበረሰብ ስብሰባዎችን እና የምርት ማሳያ መድረኮችን ማዘጋጀት፡፡
አዳዲስ ገዢዎችን (sales leads) መለየት፣ የገበያ መረጃዎችን መሰብሰብ እና ከዋናው መስሪያ ቤት ጋር በመቀናጀት ሽያጮችን መፈጸም፡፡
About You
- የቴክኒክና ጥገና ባለሙያ
ተፈላጊ መስፈርቶች፡
በኤሌክትሪክ/ኤሌክትሮኒክስ፣ ታዳሽ ኢነርጂ፣ የኢንዱስትሪ ተከላ ወይም ተዛማጅ የቴክኒክ መስኮች የቲቪኢቲ (TVET) ሰርተፍኬት (ደረጃ ||| ወይም ከዚያ በላይ) ያለው/ያላት እና ከ2 ዓመት በላይ ተግባራዊ የሶላር ተከላ እና ጥገና ልምድ ያለው/ያላት፡፡
- የሶላር ማርኬቲንግ ባለሙያ
ተፈላጊ መስፈርቶች፡
በኤሌክትሪካል፣ መካኒካል፣ በታዳሽ ኢነርጂ፣ በማርኬቲንግ ወይም ተዛማጅ መስኮች ዲፕሎማ ወይም የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ቢያንስ 2 ዓመት የሽያጭ/ማርኬቲንግ ልምድ እና ስለ ሶላር ኢነርጂ ሲስተሞች ጠንካራ ግንዛቤ ያለው/ያላት፡፡
የተለመዱ የስራ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች (ለሁለቱም የስራ መደቦች)
የስራ ጊዜ፡
6 ወራት (እንደ አፈፃፀም ብቃት የማራዘም ከፍተኛ እድል ያለው)
የስራ ቦታዎች፡
ምስራቅ ጉራጌ ዞን (ቡታጅራ አካባቢ)
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል (አርባ ምንጭ አካባቢ)
የሲዳማ ክልል አካባቢ
ኦሮሚያ ክልል (ዝዋይ፣ መቂ እና ሞጆ አካባቢዎች)
ቋንቋ እና መኖሪያ ቦታ፡
ፕሮጀክቱ የሚገነባበት አካባቢ ነዋሪ እና የአካባቢውን ቋንቋ አቀላጥፎ የሚናገር (ለአካባቢው ነዋሪዎች እና ቋንቋ ተናጋሪዎች ቅድሚያ ይሰጣል)፡፡
Requirement Skill
Teamwork and Interpersonal Skills