የጨረታ ማስታወቂያ የኤሌክትሪክ ሞተር-ሳይክል አቅርቦት/ሽያጭ

Descrição da vaga

About the Job

ኬር ህፃናትና ቤተሰብ ለኢትዮጵያ ድርጅት በምግብ ዋስትና ፕሮጀከት ሥራ እንቅስቃሴ አገልግሎት የሚሰጡ ብዛት 06/ስድስት/ የኤሌክትሪክ ሞተር-ሳይክሎችን(ELECRICAL MOTORCYCLE), አዲስ ብራንድ አስመጪና ሻጭ ኩባንያዎችን/ድርጅቶችን በጨረታ  አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የተፈላጊው የኤሌክትሪክ ሞተር-ሳይክል  ዓይነትና ይዘት/ስፔሲፊኬሽንስ፡

ባትሪው 3000-4000Watt, Lithium-ion Battery, Voltage: 76V, Discharge Current: 160A (max), Charge Current: 30A(max), Distance travel range:150-180 km in full charge, Mark/Brand:

Dinp

, ወይም

TAN-HUAWIN

, ወይም

HIWAR   HM60

የሆነ እንዲሁም:-

የተሟላ አክሰሰሪዎች

፡

ለእያንዳንዱ ሞተር-ሳይክል 1-የጭንቅላት መከላከያ/ሄልሜት፣1-የነፋስ መከላከያ፣2-ማስነሻ እና የተሟላ ሴት ቱልስ ኪት/Tools Kit set/፡፡

About You

ስለዚህ ለመጫረት የምትፈልጉ የተሸከርካሪ አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ሰነዶች ኮፒ ያሟላ የጨረታ መወዳደሪያ ፕሮፖዛላችሁን ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

እንዲሁም፡-

ተጫራች የተሸከርካሪ አስመጪና ሻጭ/አቅራቢዎች የድርጅታችሁን/ኩባንያችሁን ፕሮፋይል

የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ህጋዊ ማስረጃ ሰነድ::

ተጫራች ተጨማሪ እሴት ታክስ /15%ቫት/ ተመዝጋቢ ስለመሆኑ አገልግሎት የሚሰጥ የቫት ሰርተፊኬት

አገልግሎት የሚሰጥ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን(TIN) ሰርተፊኬት::

ከላይ ከተጠቀሱት መስፈርቶች ውስጥ አንዱንም ቢሆን ያላሟላ ተጫራች ኩባንያ/ድርጅት ከጨረታው ውድድር ይሰረዛል

የአቅርቦት/ሽያጭ  ዋጋው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ይቀርባል፡፡

አዲስ ብራንድ ተሸከርካሪዎችን በማስመጣትና በመሸጥ/በማቅረብ የመልካም ሥራ አፈጻጸም የምስክርነት ማስረጃ ያለው፡፡

አሸናፊው ሻጭ/አቅራቢ የተፈለገውን የሱዙኪ ሞተርሳይክል የሚያቀርብበት ጊዜ በትክክል ይገለጽ፡፡

ተጫራቹ ይህ ጨረታ

በኢትዮ ጆብ ማህበራዊ ሚዲያ/የጨረታ ማስታወቂያ ድረ-ገፅ

(

www.Ethiojobs.net

)

BID advertisement  ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የምታቀርቡበትን ዋጋ ከተሟላ ህጋዊ ማስረጃዎቻችሁ/ሰነድ ጋር መደበኛ ክፍት የስራ ቀናት እስከ ህዳር 18/2019 ዓ.ም

አርብ

ዕለት ከጠዋቱ 5:45ሰዓት ድረስ በኢንቨሎፕ ወይም በፖስታ አሽገው አዲስ አበባ-ቦሌ መድሃኒአለም ቤተ-ክርስቲያን ጀርባ በሚገኘው የቻይልድ ፈንድ ኢትዮጵያ ድርጅት ብሔራዊ ቢሮ- እንግዳ መቀበያ/ሪሴፕሽን  በአካል በመቅረብ ማስቀመጥ ይጠበቅባችኋል፡፡

ጨረታዉ በቀን፦ ህዳር 18/2019 ዓ.ም

አርብ

ዕለት ከጠዋቱ 5:45 ሰዓት ላይ ያበቃል፡፡ እንዲሁም ጨረታው በዕለቱ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት በዚያው የቻይልድ ፈንድ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቢሮ- አዲስ አበባ ድርጅቱ ቅጥር ግቢ ተጫራቾች ወይም  ተወካዮቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ  ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

Requirement Skill

Communication

Attention to detail

Como se candidatar

ተጫራቹ ይህ ጨረታ

በኢትዮ ጆብ ማህበራዊ ሚዲያ/የጨረታ ማስታወቂያ ድረ-ገፅ

(

www.Ethiojobs.net

)

BID advertisement  ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የምታቀርቡበትን ዋጋ ከተሟላ ህጋዊ ማስረጃዎቻችሁ/ሰነድ ጋር መደበኛ ክፍት የስራ ቀናት እስከ ህዳር 18/2019 ዓ.ም

አርብ

ዕለት ከጠዋቱ 5:45ሰዓት ድረስ በኢንቨሎፕ ወይም በፖስታ አሽገው አዲስ አበባ-ቦሌ መድሃኒአለም ቤተ-ክርስቲያን ጀርባ በሚገኘው የቻይልድ ፈንድ ኢትዮጵያ ድርጅት ብሔራዊ ቢሮ- እንግዳ መቀበያ/ሪሴፕሽን  በአካል በመቅረብ ማስቀመጥ ይጠበቅባችኋል፡፡

አድራሻ

፡-

ኬር ህፃናትና ቤተሰብ ለኢትዮጵያ ድርጅት%ቡኢ ከተማ 'ሶዶ ወረዳ'ጉራጌ ዞን'ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ-ምዕራብ አቅጣጫ 103ኪ.ሜ በአለምገና-ቡታጅራ/ሆሳና ዋናው አስፋልት መንገድ፡፡

የስልክ ቁጥር፡

0468830023

An error has occurred. This application may no longer respond until reloaded. Reload 🗙