About the Job
ኬር ህፃናትና ቤተሰብ ለኢትዮጵያ ድርጅት በምግብ ዋስትና ፕሮጀከት ሥራ እንቅስቃሴ አገልግሎት የሚሰጡ ብዛት 06/ስድስት/ የኤሌክትሪክ ሞተር-ሳይክሎችን(ELECRICAL MOTORCYCLE), አዲስ ብራንድ አስመጪና ሻጭ ኩባንያዎችን/ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የተፈላጊው የኤሌክትሪክ ሞተር-ሳይክል ዓይነትና ይዘት/ስፔሲፊኬሽንስ፡
ባትሪው 3000-4000Watt, Lithium-ion Battery, Voltage: 76V, Discharge Current: 160A (max), Charge Current: 30A(max), Distance travel range:150-180 km in full charge, Mark/Brand:
Dinp
, ወይም
TAN-HUAWIN
, ወይም
HIWAR HM60
የሆነ እንዲሁም:-
የተሟላ አክሰሰሪዎች
፡
ለእያንዳንዱ ሞተር-ሳይክል 1-የጭንቅላት መከላከያ/ሄልሜት፣1-የነፋስ መከላከያ፣2-ማስነሻ እና የተሟላ ሴት ቱልስ ኪት/Tools Kit set/፡፡
About You
ስለዚህ ለመጫረት የምትፈልጉ የተሸከርካሪ አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ሰነዶች ኮፒ ያሟላ የጨረታ መወዳደሪያ ፕሮፖዛላችሁን ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
እንዲሁም፡-
ተጫራች የተሸከርካሪ አስመጪና ሻጭ/አቅራቢዎች የድርጅታችሁን/ኩባንያችሁን ፕሮፋይል
የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ህጋዊ ማስረጃ ሰነድ::
ተጫራች ተጨማሪ እሴት ታክስ /15%ቫት/ ተመዝጋቢ ስለመሆኑ አገልግሎት የሚሰጥ የቫት ሰርተፊኬት
አገልግሎት የሚሰጥ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን(TIN) ሰርተፊኬት::
ከላይ ከተጠቀሱት መስፈርቶች ውስጥ አንዱንም ቢሆን ያላሟላ ተጫራች ኩባንያ/ድርጅት ከጨረታው ውድድር ይሰረዛል
የአቅርቦት/ሽያጭ ዋጋው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ይቀርባል፡፡
አዲስ ብራንድ ተሸከርካሪዎችን በማስመጣትና በመሸጥ/በማቅረብ የመልካም ሥራ አፈጻጸም የምስክርነት ማስረጃ ያለው፡፡
አሸናፊው ሻጭ/አቅራቢ የተፈለገውን የሱዙኪ ሞተርሳይክል የሚያቀርብበት ጊዜ በትክክል ይገለጽ፡፡
ተጫራቹ ይህ ጨረታ
በኢትዮ ጆብ ማህበራዊ ሚዲያ/የጨረታ ማስታወቂያ ድረ-ገፅ
(
www.Ethiojobs.net
)
BID advertisement ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የምታቀርቡበትን ዋጋ ከተሟላ ህጋዊ ማስረጃዎቻችሁ/ሰነድ ጋር መደበኛ ክፍት የስራ ቀናት እስከ ህዳር 18/2019 ዓ.ም
አርብ
ዕለት ከጠዋቱ 5:45ሰዓት ድረስ በኢንቨሎፕ ወይም በፖስታ አሽገው አዲስ አበባ-ቦሌ መድሃኒአለም ቤተ-ክርስቲያን ጀርባ በሚገኘው የቻይልድ ፈንድ ኢትዮጵያ ድርጅት ብሔራዊ ቢሮ- እንግዳ መቀበያ/ሪሴፕሽን በአካል በመቅረብ ማስቀመጥ ይጠበቅባችኋል፡፡
ጨረታዉ በቀን፦ ህዳር 18/2019 ዓ.ም
አርብ
ዕለት ከጠዋቱ 5:45 ሰዓት ላይ ያበቃል፡፡ እንዲሁም ጨረታው በዕለቱ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት በዚያው የቻይልድ ፈንድ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቢሮ- አዲስ አበባ ድርጅቱ ቅጥር ግቢ ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
Requirement Skill
Communication
Attention to detail