በምትተኙበት ጊዜ የስራ እድል የሚያመጣልዎ አዲሱ የ Wrkzon Job Agent (AI + Human Co-pilot) አሰራር
እርሶ በተኛችሁበት፣ በሚያረፉበት ወይም በሌላ ስራ ላይ በሆናችሁበት ሰዓት ለእርሶ የሚሆኑ የስራ እድሎችን የሚፈልግ፣ ማመልከቻዎችን የሚልክ እና እስከ ቃለ-መጠይቅ የሚያደርሳችሁ አገልግሎት ቢኖር ህይወትዎ ምን ያህል ይቀለል ነበር?
በ Wrkzon የቀረበው አዲሱ Job Agent (Wrkzon Agency) የ AI ፈጣን ቴክኖሎጂን ከሙያተኞች (Human Experts) ድጋፍ ጋር በማቀናጀት የስራ ፍለጋ ጉዞዎን ሙሉ በሙሉ አውቶሜት የሚያደርግ ድንቅ አገልግሎት ነው
በዛሪው ብሎግ የ Wrkzon Job Agent ምን እንደሆነ፣ እንዴት እንደሚሰራ እና እርስዎ ደረጃ በደረጃ ተጠቅመው እንዴት አሸናፊ መሆን እንደሚችሉ በዝርዝር እናቀርባለን።
1. Wrkzon Job Agent (Agency) ምንድነው ?
Wrkzon Job Agent የእርስዎን የካሪየር ግብ መሰረት በማድረግ ስራዎችን የሚያስስ፣ CVዎን ለሚፈልጉት የስራ አይነት አስተካክሎ (Tailor አድርጎ) የሚያመልክት እና ለቃለ-መጠይቅ (Interview) የሚያዘጋጅ የእርስዎ "Personal Career Co-pilot" ነው።
ይህ ሲስተም "AI Speed + Human Experts" የተሰኘውን የላቀ አሰራር ይከተላል፦
በ AI ፍጥነት (AI Speed): በ 24 ሰዓት ውስጥ የሚወጡ አዳዲስ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ የሪሞት ስራዎችን በፍጥነት ያሰሳል፣ CVዎን ከስራ መደቡ ጋር እንዲጣጣም ያዘጋጃል
በሙያተኞች ክትትል (Human Experts): የ Wrkzon የካሪየር ባለሙያዎች እያንዳንዱ ማመልከቻ በትክክል መላኩን እና የቃለ-መጠይቅ ዝግጅትዎን በቅርበት ይከታተላሉ።
2. Wrkzon Job Agent እንዴት ይሰራል? (How It Works)
አገልግሎቱ ከስራ ፍለጋ አላማዎ ተነስቶ እስከ ተቀጣሪነት ደረጃ የሚያደርስ አምስት (5) ዋና ዋና ደረጃዎችን ይከተላል ፦
የሚፈልጉትን የስራ መደብ፣ ቦታ (ሀገር ውስጥ ወይም Remote) እና የሚፈልጉትን የደመወዝ መጠን ይግለጹ።
AI እና የካሪየር ባለሙያዎች ስራዎችን ይቃኛሉ፣ CVዎን ያስተካክላሉ፣ ማመልከቻዎችን ያለማቋረጥ ያዘጋጃሉ።
የማመልከቻዎችዎን ሂደት በዳሽቦርድዎ ላይ በ Real-time እየተከታተሉ የቃለ-መጠይቅ ጥሪዎችን በቀጥታ ይቀበላሉ።
1-ለ-1 የቃለ-መጠይቅ ልምምዶች፣ Mock Sessions እና ስትራቴጂካዊ የምክር አገልግሎት ያገኛሉ።
የደመወዝ ድርድር እገዛ እና ስራ እስከሚጀምሩበት ቀን ድረስ ሙሉ ድጋፍ ይደረግልዎታል።
3. አጠቃቀሙ ደረጃ በደረጃ (Step-by-Step Guide)
አዲሱን አገልግሎት ለመጀመር እና የሩጫው ተሳታፊ ለመሆን የሚከተሉትን ቀላል ደረጃዎች ይከተሉ፦
ደረጃ 1፦ ወደ ሊንኩ ይግቡ
በመጀመሪያ በሊንኩ አድራሻ https://www.wrkzon.com/agency በመግባት የ Wrkzon Agent ገጽን ይክፈቱ።
ደረጃ 2፦ Waitlist ን ይቀላቀሉ (Join the Waitlist)
በገጹ ላይ የሚገኘውን "Join the waitlist" የሚለውን ብርቱካናማ በተን ይጫኑ። አገልግሎቱ በ Beta ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ነጻ (Free while in beta) ነው።
ደረጃ 3፦ የካሪየር ፍላጎትዎን ይሙሉ
አካውንትዎ ውስጥ በመግባት የሚከተሉትን መረጃዎች ያስገቡ፦
የሚፈልጉት የሙያ መስክ (ለምሳሌ፡ Senior .NET Dev, Digital Marketer, Data Analyst)
የስራው ቦታ አማራጭ (Remote, Hybrid, ወይም On-site)
የሚጠብቁት የደመወዝ መጠን
ደረጃ 4፦ ሂደቱን በ Live Dashboard ይከታተሉ
አንዴ ከተመዘገቡ በኋላ Wrkzon Agent Activity ዳሽቦርድ ላይ የሚከተሉትን ሂደቶች በቀጥታ ማየት ይችላሉ ፦
ኤጀንቱ ያመለከተላችሁን ስራዎች (ለምሳሌ፦ Applied to Senior .NET Dev at TechCorp)
ለእያንዳንዱ ስራ የተዘጋጀውን የተስተካከለ CV (Tailored resume for Automation Lead)
የተላኩልዎትን የቃለ-መጠይቅ ጥሪዎች (Interview requests pending)
አሁኑኑ ይጀምሩ
የስራ ማስታወቂያዎችን በየቀኑ የመፈለግ፣ CVን በየጊዜው ማስተካከል እና መላክ ሰልችቶዎታል? Wrkzon Job Agent ይህንን አሰልቺ ሂደት አውቶሜት በማድረግ በእርሶ ምትክ ቀንና ሌሊት ስራውን ያከናውናል ።
አሁኑኑ በነጻ ይመዝገቡ፦ https://www.wrkzon.com/agency
የተረጋገጡ አዳዲስ ስራዎችን ለማየት፦ Wrkzon Jobs ላይ ይመልከቱ።

Comments (0)
No comments yet. Be the first to comment!